Friday, November 30, 2018

በመቐለ ዩኒቨርስቲ ለድህረ ምረቃ ተማሪዎች ቅበላ ተደረገ።


#መቐለ_ዩኒቨርስቲ
ከሶማሊላንድ ሀርጌሳ ዩኒቨርስቲ ለድህረ ምረቃ ትምህርት ለመጡ ተማሪዎች ደማቅ ኣቀባበል ተደረገ።
*******************************
የድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን ለመከታተል ከሶማሊላንድ ሃርጌሳ ዩኒቨርስቲ ለመጡ 68 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ህዳር 20፣ የመቐለ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ በተገኙበት በቃላሚኖ ግቢ ደማቅ ኣቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን የኮሌጁ ዲን ደ.ር በሪሁ ገብረኪዳን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ኣስተላልፈዋል። 
          የኣካዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር ደ.ር ታደሰ እንደገለፁት ዩኒቨርስቲያችን በኣጠቃላይ 333 የትምህርት ፕሮግራሞች እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን ከሀገራችን ግብርና ወደ ኢንዳስትሪ መር በሚደረገው ሽግግር እጅግ ኣስፈላጊ እና በመቐለ ዩኒቨርስቲ ብቻ የሚሰጡ (ካይዘን ኢንስቲትዩት፥ ክላይሜት ሜትሮሎጂ፣ ፔትሮሊየም ኢንጂነሪንግ) ጨምሮ በኣለም ኣቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እና በርካታ የማህበረሰብ ችግሮች በሚፈቱ (Need Based Diversification) 40 የPHD ፕሮግራሞች እየሰጠ ይገኛል። 20ዎቹ በዚሁ ኣመት የተጀመሩ ፕሮግራሞች ናቸው። 
                ዩኒቨርስቲው ከሶማሊላንድ መንግስት፣ከምስራቅ ኣፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት(IGAD)፥ ደቡብ ሱዳን፥ጋና እና ሌሎች ሀገሮች ጨምሮ በርካታ ተማሪዎች እያስተናገደ ይገኛል። 
ኣዘጋጅ፥ ግደይ ልኡል