Friday, December 20, 2019

Thank You to our Conference Attendees

Dear Attendee
On behalf of the Mekelle University Alumni Director Office, we want to thank you for attending the 2nd Annual Conference under the theme "Our Alumni Engagement for Mekelle University Excellence" on December 14- 2019 at AddisAbaba.


We hope that you found the conference informative and worthwhile. The primary goal of this conference was to bring us together under one umbrella and making great get together as well as friends and partners from all over Ethiopia in an open dialogue, under one roof to discuss the issues on making strong bond relationship with our notable alumni and mekelle University.
Besides, developing possible strategies to share and contribute your role in the remarkable progress of our university and the need to more engaged in initiatives taking place together.
We believe that your diverse and dynamic professionalism provided in-depth insight, as well as, actionable and practical engagement able to share and become more effective in the on-going development efforts of Mekelle University.
Your presence helped to make this event a great success and your enthusiasm and positive spirit helped make our time together both productive and fun. Your honored comments suggestions were worthy enough feedback for what we are doing. We wish you all the best and hope that you continue to get in touch together.
Our Alumni Our Pride!
Mekelle University Alumni Directorate Office

Friday, December 13, 2019

በሁለተኛው የመቐለ ዩኒቨርስቲ አልሙናይ ኮንፈረስ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ።

"............የቀድሞ  ምሩቃን በዩኒቨርስቲያችን ሁለንተናዊ እድገት ከጎን እንዲቆሙ እንዲሁም እንደ ዩኒቨርሲቲ ለነሱ መፍጠር የምንችለው እድል የተጀመረ አካሄድ ኣለ።"
                    ኣቶ ጎይትኦም ተገኝ ፣ የመቐለ ዩኒቨርስቲ ኣለማቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክተር



ለሁለተኛ ግዜ በአዲስ አበባው ከተማ ሃርመኒ ሆቴል " የአልሙናይ ተሳትፎ ለመቐለ ዩኒቨርስቲ ለላቐ ውጤት" በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው የመቐለ ዩኒቨርስቲ አልሙናይ መድረክ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።
      የመድረኩ አስፈላጊነት በተመለከተ ከቀድሞ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚደረጉ ግንኝነቶች ተቋማዊ አካሄድ እንዲኖር እና ዩኒቨርስቲው በሚሰራቸው ስራዎች የራሳቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉና ተመርቀው ከወጡ በኋላም ከዩኒቨርስቲው ጋር ያላቸው ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚረዳና ከ90,000 የዩኒቨርስቲያችን የቀድሞ ምሩቃን በጋራ ተባብረን ለመስራት ይህን ኮንፈረንስ በቀጣይነት ለሚደረጉ ጉልህ ሚና እንደለው የመቐለ ዩኒቨርስቲ የዓለማቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ጎይትኦም ተገኝ ገልፀዋል።
    
ዳይሬከተሩ አክለውም " ከዚህ በፊት የተወሰኑ አመታት ጥረት ስናደርግለት ቆይተን በቅርቡ ባቋቋምነው የአልሙናይ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ፅ/ቤት በርካታ ስራዎች ስንሰራ ቆይተናል። አምና  ለመጀመሪያ ግዜ ባዘጋጀነው ኮንፈረንስ ብዙ ግብአት የወሰድንበት ሲሆን አሁን በአዲስ አበባ ከተማ በምናዘጋጀው የምክክር መድረክ ይበልጥ ተቀራርበን በጋራ ለመስራት የሚያስችል ልዩ አጋጣሚ ነው።"

    መቐለ ዩኒቨርስቲ በአለማቀፍ ግንኙነት ማጠናከር ዙርያ በሚያደርገው ጉዞ ተቋማዊ የሆነ አወቃቀር የተቋቋመው የአልሙናይ ዳይሬክቶሬት ፅ/ቤቱ ከ90,000 በላይ የዩኒቨርስቲው ምሩቃን በዩኒቨርስቲው ሁለንተናዊ እድገት ከጎን እንዲቆሙ እንዲሁም እንደ ዩኒቨርሲቲ ለነሱ መፍጠር የምንችለው እድል የተጀመረ አካሄድ እንዳለ አቶ ጎይትኦም አስረድተዋል።

     የቀድሞ የዪኒቨርስቲው ተማሪዎች እና በዩኒቨርስቲው መካከል የህይወት ዘመን ግንኙነት እንዲፈጠር፤ የመረጃ እና የእውቀት ሽግግር እንዲኖር፤ ዩኒቨርስቲው በሚሰራቸው ስራዎች የቀድሞ ተማሪዎች አሻረው እንዲያሳርፉ በዋናነት እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን ባለፈው አንድ አመትም የተለያዩ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን በአዲስ አበባ የሚካሄው የዘንድሮ መድረክም "የቀድሞ ምሩቃን ተሳትፎ ለመቐለ ዩኒቨርስቲ የላቀ ውጤት" በሚል መሪቃል እንደሚከበር የአልሙናይ ዳይሬክተር ፅ/ቤቱ አስተባባሪ አቶ ኢፍሬም ሰይፉ ገልፀዋል።

የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት ጨምሮ ሌሎች የዩቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Sunday, February 24, 2019

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህክምና ተማሪዎች 10ኛ ዙር ምረቃ እና የጥርስ ህክምና ተማሪዎች 2ኛ ዙር ምረቃ በደማቅ ሁኔታ አስመርቅዋል።

                                                                                                                                                       
 መቐለ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህክምና ተማሪዎች 10ኛ ዙር ምረቃ እና የጥርስ ህክምና ተማሪዎች 2ኛ ዙር ምረቃ  ቅዳሜ የካቲት 16-2011 ዓ/ም  በደማቅ ሁኔታ አስመርቅዋል።

ዩኒቨርሲቲው በአጠቃላይ 376 ተማሪዎች ያስመረቀ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 245 በመጀመርያ ዲግሪ (ዶክትሬት)፣ 78 በድህረ-ምረቃ፣ ስፔሻሊቲ በተለያዩ የህክምና ዘርፎች ያስመረቀ ሲሆን ከአጠቃላይ ተመራቂዎች 97 ሴት ተመራቂዎች ናቸው።
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት የኢፌዴሪ የህ/ተ/ም/ቤት አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት፣ አዳዲስ እና ነባር የቦርድ አባላት በምርቃት ስነ ከስርዓቱ ተገኝተው የእንኳን ደስ አላቹሁ መልእክታቸው ያስተላለፋ ሲሆን  መቐለ ዩኒቨርሲቲ የሴኔት አባላት፣ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ስራ ሃላፊዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረስብ እና ውድ የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኘበት የምርቃት መርሃ  ግብሩ በደማቅ ሁኔታ ተካሂድዋል።
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ለተመራቂዎችና ቤተሰቦቻቸው እንኳን ደስ አላችሁ እያለ መልካም የስራ ዘመን ይመኛል።
            ለካቲት 16፣2011ዓ.ም






Wednesday, December 26, 2018

Drop of Water Club has Provided 45 Installed water pumps for the Society.

        Mekelle University lays more emphasis for the Students Association, Clubs and Committees By effectively organizing Volunteers  so as to Serve for the Surrounding Society.
      Drop of water Club was established before 5 years and By organizing its More than 2300 volunteer members is making difference in the Countryside as well cross-region Measurable and Much Significance Results.
     The Club has built 45 water pumps for the Remote society, 40 of them are in Tigray and 5 in Amhara Regional Governments Over the years. Undergoing Constructions also In
                                                                                             -Tigray 3,
                                                                                              -Amhara 5 ,
                                                                                               -Oromiya 1,
                                                                                                 -Harar 1 and Guragie zone 1 water pumps are going Ongoing Construction in collaboration with partner non-Governmental organization.


This club also is making awareness on Menstruation Hygiene Management (MHM) for more tthan 369 mothers and sisters donating Modest and pants. 


Saturday, December 22, 2018

የዓይደር ግቢ ተማሪዎች ፓርላማ የሩብ ኣመት ጠቅላላ ጉባኤ ኣካሄደ።

      የዓይደር ግቢ ተማሪዎች ፓርላማ የሩብ ኣመት ጠቅላላ ጉባኤ የኮለጁን ኣመራሮች እና ከእያንዳንዱ የተማሪዎች ኣደረጃጀቶች ተወካዮች በተጋባዥ እንግዳነት በተገኙበት ለሁለተኛ ግዜ ስብሰባዉን ኣካሂደዋልበዚህ ስብሰባም ባለፉት 3 ወራት በህብረቱ የተሰሩትን ሥራዎች በቀረበው ሪፖርት  የነበሩት የኣፈፃፀም እንቅስቃሴ ግምገማ ከተካሄደ በኋላ በግቢው ኣመራሮች ሰፋ ያለ መግለጫ(ንጝር) ተደርጎዋል።  

       እንዲሁም  የስራ ዘመናቸው የጨረሱ ነባር የስራ ኣስፈፃሚ ኣባላት የነበራቸው ልምድ ለፓርላማው ካካፈሉ በኃላ በክብር ሽኝት ተደርጎላቿል፥፥ ኣዲስ 2 የስራ ኣስፈፃሚዎች (የህብረት ኣባላት) በማስመረጥ ስብሰባውን ኣጠናቀዋል።

ታህሳስ 12፣2011ዓ.ም


Saturday, December 15, 2018

መቐለ ዩኒቨርስቲ ከትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በመተባበር በሀገራችን ወቅታዊ የፖለቲካ ምጣኔ ሀብታዊ እና ማሕበራዊ ያተኮረ ኮንፈረንስ እያካሄደ ይገኛል።


መቐለ ዩኒቨርስቲ ከትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በመተባበር ምሁራን፣ የሃይማኖት ኣባቶች፣ የመንግስት ከፍተኛ ኣመራር፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኣመራር፣ የመቐለ ከተማ ኣስተዳደር ፅ/ቤት ተወካዮች እና የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ያሳተፈ በሀገራችን ወቅታዊ የፖለቲካ ምጣኔ ሀብታዊ እና ማሕበራዊ ያተኮረ የሁለት ቀን ኮንፈረንስ እያካሄደ ይገኛል።