Friday, December 13, 2019

በሁለተኛው የመቐለ ዩኒቨርስቲ አልሙናይ ኮንፈረስ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ።

"............የቀድሞ  ምሩቃን በዩኒቨርስቲያችን ሁለንተናዊ እድገት ከጎን እንዲቆሙ እንዲሁም እንደ ዩኒቨርሲቲ ለነሱ መፍጠር የምንችለው እድል የተጀመረ አካሄድ ኣለ።"
                    ኣቶ ጎይትኦም ተገኝ ፣ የመቐለ ዩኒቨርስቲ ኣለማቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክተር



ለሁለተኛ ግዜ በአዲስ አበባው ከተማ ሃርመኒ ሆቴል " የአልሙናይ ተሳትፎ ለመቐለ ዩኒቨርስቲ ለላቐ ውጤት" በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው የመቐለ ዩኒቨርስቲ አልሙናይ መድረክ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።
      የመድረኩ አስፈላጊነት በተመለከተ ከቀድሞ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚደረጉ ግንኝነቶች ተቋማዊ አካሄድ እንዲኖር እና ዩኒቨርስቲው በሚሰራቸው ስራዎች የራሳቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉና ተመርቀው ከወጡ በኋላም ከዩኒቨርስቲው ጋር ያላቸው ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚረዳና ከ90,000 የዩኒቨርስቲያችን የቀድሞ ምሩቃን በጋራ ተባብረን ለመስራት ይህን ኮንፈረንስ በቀጣይነት ለሚደረጉ ጉልህ ሚና እንደለው የመቐለ ዩኒቨርስቲ የዓለማቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ጎይትኦም ተገኝ ገልፀዋል።
    
ዳይሬከተሩ አክለውም " ከዚህ በፊት የተወሰኑ አመታት ጥረት ስናደርግለት ቆይተን በቅርቡ ባቋቋምነው የአልሙናይ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ፅ/ቤት በርካታ ስራዎች ስንሰራ ቆይተናል። አምና  ለመጀመሪያ ግዜ ባዘጋጀነው ኮንፈረንስ ብዙ ግብአት የወሰድንበት ሲሆን አሁን በአዲስ አበባ ከተማ በምናዘጋጀው የምክክር መድረክ ይበልጥ ተቀራርበን በጋራ ለመስራት የሚያስችል ልዩ አጋጣሚ ነው።"

    መቐለ ዩኒቨርስቲ በአለማቀፍ ግንኙነት ማጠናከር ዙርያ በሚያደርገው ጉዞ ተቋማዊ የሆነ አወቃቀር የተቋቋመው የአልሙናይ ዳይሬክቶሬት ፅ/ቤቱ ከ90,000 በላይ የዩኒቨርስቲው ምሩቃን በዩኒቨርስቲው ሁለንተናዊ እድገት ከጎን እንዲቆሙ እንዲሁም እንደ ዩኒቨርሲቲ ለነሱ መፍጠር የምንችለው እድል የተጀመረ አካሄድ እንዳለ አቶ ጎይትኦም አስረድተዋል።

     የቀድሞ የዪኒቨርስቲው ተማሪዎች እና በዩኒቨርስቲው መካከል የህይወት ዘመን ግንኙነት እንዲፈጠር፤ የመረጃ እና የእውቀት ሽግግር እንዲኖር፤ ዩኒቨርስቲው በሚሰራቸው ስራዎች የቀድሞ ተማሪዎች አሻረው እንዲያሳርፉ በዋናነት እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን ባለፈው አንድ አመትም የተለያዩ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን በአዲስ አበባ የሚካሄው የዘንድሮ መድረክም "የቀድሞ ምሩቃን ተሳትፎ ለመቐለ ዩኒቨርስቲ የላቀ ውጤት" በሚል መሪቃል እንደሚከበር የአልሙናይ ዳይሬክተር ፅ/ቤቱ አስተባባሪ አቶ ኢፍሬም ሰይፉ ገልፀዋል።

የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት ጨምሮ ሌሎች የዩቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

No comments:

Post a Comment