መቐለ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህክምና ተማሪዎች 10ኛ ዙር ምረቃ እና የጥርስ ህክምና ተማሪዎች 2ኛ ዙር ምረቃ ቅዳሜ የካቲት 16-2011 ዓ/ም በደማቅ ሁኔታ አስመርቅዋል።
ዩኒቨርሲቲው በአጠቃላይ 376 ተማሪዎች ያስመረቀ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 245 በመጀመርያ ዲግሪ (ዶክትሬት)፣ 78 በድህረ-ምረቃ፣ ስፔሻሊቲ በተለያዩ የህክምና ዘርፎች ያስመረቀ ሲሆን ከአጠቃላይ ተመራቂዎች 97 ሴት ተመራቂዎች ናቸው።
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት የኢፌዴሪ የህ/ተ/ም/ቤት አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት፣ አዳዲስ እና ነባር የቦርድ አባላት በምርቃት ስነ ከስርዓቱ ተገኝተው የእንኳን ደስ አላቹሁ መልእክታቸው ያስተላለፋ ሲሆን መቐለ ዩኒቨርሲቲ የሴኔት አባላት፣ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ስራ ሃላፊዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረስብ እና ውድ የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኘበት የምርቃት መርሃ ግብሩ በደማቅ ሁኔታ ተካሂድዋል።
No comments:
Post a Comment