Gidey Leul Perspective's

እንኳን በደህና መጡ።

Wednesday, December 26, 2018

Drop of Water Club has Provided 45 Installed water pumps for the Society.

        Mekelle University lays more emphasis for the Students Association, Clubs and Committees By effectively organizing Volunteers  so as to Serve for the Surrounding Society.
      Drop of water Club was established before 5 years and By organizing its More than 2300 volunteer members is making difference in the Countryside as well cross-region Measurable and Much Significance Results.
     The Club has built 45 water pumps for the Remote society, 40 of them are in Tigray and 5 in Amhara Regional Governments Over the years. Undergoing Constructions also In
                                                                                             -Tigray 3,
                                                                                              -Amhara 5 ,
                                                                                               -Oromiya 1,
                                                                                                 -Harar 1 and Guragie zone 1 water pumps are going Ongoing Construction in collaboration with partner non-Governmental organization.


This club also is making awareness on Menstruation Hygiene Management (MHM) for more tthan 369 mothers and sisters donating Modest and pants. 


Posted by Mekelle University Alumni Director Office at 2:20 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Saturday, December 22, 2018

የዓይደር ግቢ ተማሪዎች ፓርላማ የሩብ ኣመት ጠቅላላ ጉባኤ ኣካሄደ።

      የዓይደር ግቢ ተማሪዎች ፓርላማ የሩብ ኣመት ጠቅላላ ጉባኤ የኮለጁን ኣመራሮች እና ከእያንዳንዱ የተማሪዎች ኣደረጃጀቶች ተወካዮች በተጋባዥ እንግዳነት በተገኙበት ለሁለተኛ ግዜ ስብሰባዉን ኣካሂደዋል። በዚህ ስብሰባም ባለፉት 3 ወራት በህብረቱ የተሰሩትን ሥራዎች በቀረበው ሪፖርት  የነበሩት የኣፈፃፀም እንቅስቃሴ ግምገማ ከተካሄደ በኋላ በግቢው ኣመራሮች ሰፋ ያለ መግለጫ(ንጝር) ተደርጎዋል።  

       እንዲሁም  የስራ ዘመናቸው የጨረሱ ነባር የስራ ኣስፈፃሚ ኣባላት የነበራቸው ልምድ ለፓርላማው ካካፈሉ በኃላ በክብር ሽኝት ተደርጎላቿል፥፥ ኣዲስ 2 የስራ ኣስፈፃሚዎች (የህብረት ኣባላት) በማስመረጥ ስብሰባውን ኣጠናቀዋል።

ታህሳስ 12፣2011ዓ.ም


Posted by Mekelle University Alumni Director Office at 4:06 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Saturday, December 15, 2018

መቐለ ዩኒቨርስቲ ከትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በመተባበር በሀገራችን ወቅታዊ የፖለቲካ ምጣኔ ሀብታዊ እና ማሕበራዊ ያተኮረ ኮንፈረንስ እያካሄደ ይገኛል።


መቐለ ዩኒቨርስቲ ከትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በመተባበር ምሁራን፣ የሃይማኖት ኣባቶች፣ የመንግስት ከፍተኛ ኣመራር፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኣመራር፣ የመቐለ ከተማ ኣስተዳደር ፅ/ቤት ተወካዮች እና የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ያሳተፈ በሀገራችን ወቅታዊ የፖለቲካ ምጣኔ ሀብታዊ እና ማሕበራዊ ያተኮረ የሁለት ቀን ኮንፈረንስ እያካሄደ ይገኛል።
     


Posted by Mekelle University Alumni Director Office at 7:53 AM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Friday, December 14, 2018

በመ.ቴ.ኢ ግቢ ለተመራቂ ተማሪዎች ስልጠና ተሰጠ።

በመቐለ ዩኒቨርስቲ የስራ ማእከል ዳይሬክተር ፅ/ቤት የተዘጋጀ የኣቅም ግንባታ ስልጠና ለተመራቂ ተማሪዎች ታህሳስ 3,2011ዓ.ም በመ.ቴ.ኢ ግቢ ተሰጥቷል።
         በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጽ/ቤቱ ዳይሬክተር ደ/ር ግርማይ እንደገለጹት በተያዘው ኣመት በተመራቂ ተማሪዎች ዘርፈ ብዙ የክህሎት ማሳደጊያ ስልጠናዎች እና የስራ ፈጠራ ተሞክሮዎች  በመስጠት ተወዳዳሪ እና ብቃት ያላቸው ተማሪዎች  ለማፍራት እንዲሁም ለኣጋር ካምፓኒዎች ተቋማት እንዲጎበኙ ክፍት ለማድረግ ዝግጅታችን ጨርሰናል ብለዋል። ኣክለውም የካሬር ችለብ በዚህ ወር ይቋቋማል።።

          ስልጠናው መሰረታዊ የክህሎት ማዳበር በማተኮር በcv ኣጻጻፍ፣ የኣፕሊኬሽን ደብዳቤ ኣዘገጃጀት እና ቃለ መጠይቅ ኣቀራረብ ዙርያ በወ/ሮ ብርሃን የፅ/ቤቱ መማክርቱ ሰፊ ስልጠና የሰጡ ሲሆን የካሬር እና ጆብ ፌር መድረኮች በማዘጋጀት፣ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች በተለያዩ የኢንተርኔት ስኮላር ሺፖች እና ፈለውሽፖች የሚያመለክቱበትና የሚወዳደሩበት የክህሎት ስልጠናዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።
         ይህ የክህሎት ግንባታ ስልጠና ለ2ኛ ግዜ ሲሆን ለቅዳሜ ታህሳስ 6,2011ዓ.ም ደግሞ በቃላሚኖ ግቢ ለሚገኙ ተመራቂ ተማሪዎች የሚቀጥል ይሆናል።













መቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት
Posted by Mekelle University Alumni Director Office at 10:29 AM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Thursday, December 13, 2018

የኤች.ኣይ.ቪ/ኤድስ ሳምንት በመቐለ ዩኒቨርስቲ እየተከበረ ይገኛል በዓሉ በማስመልከት መልእክት ተላልፏል።።


ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ኤች አይ ቪ ኤድስ እና ስነ ተዋልዶ ጤና ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የዓለም ኤደስ ቀን ምክንያት በማድረግ ለተማሪዎች እና ዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ የተላለፈ መልዕክት
በመጀመሪያ ዉድ ተማሪዎቻችን እንኳን ለ2011 ዓ.ም በሰላም አረሳችሁ እንዲሁም ወደ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በደህና መጣችሁ!
ህዳር 22 (December 1) የዓለም ኤድስ ቀን እየተባለ በዓለምና በአገር አቀፍ ደረጃ እንደሚከበር ይታወቃል፡፡  ስለሆነም  በ2011 ዓ.ም ወይም 2018 በአሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ‘’Know Your Status!’’ በሚል መሪ ቃል ለ 30ኛ ጊዜ ሲከበር በኣገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ‘’ለኤች አይ ቪ ይበልጥ ተጋላጭ ነን፤ እንመርመር ራሳችንን እንወቅ !’’ በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡ የበአሉ መሪ ቃል እንደሚያመለክተዉ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በፈቃደኝነት የኤች አይ ቪ ደም ምርመራ በማድረግ እያዳንዱ ሰዉ ያለበትን ሁኔታ ማወቅ አለበት ማለት ነዉ፡፡
በዩኒቨርሲቲያችን ደረጃ የዘንድሮዉን የዓለም ኤድስ ቀን በየግቢዎቻችን በአስተባባሪዎቻችንና በአቻ ለአቻ ተማሪዎች ክለብ በኩል የተለያዩ የህትመት ዉጤቶችን በመጠቀም አስተማሪ መልዕክቶችን እያስተላለፍን በአሉን እያከበረን እንገኛለን፡፡
በአሁኑ ወቅት በአገር አቀፍ ደረጃ በኤ ች አይ ቪ እና ስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች መከላከል እና መቆጣጠር ስራዎች የመዘናጋት አዘማሚያ ይታያል፡፡ ነገር ግን ይህ ማለት ኤች አይ ቪ የለም  ወይም ጠፍቷል ማለት እንዳልሆነ ለተማሪዎቻችና የዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ ለማሳሰብ እወዳለሁ፡፡ አንዳንድ በአገር አቀፍ ደረጃ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት የቫይረሱ ስርጭት እንደገና እያገረሸ እና አዳዲስ በቫይረሱ የተጠቁ ወገኞች ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ ያመለክታሉ፡፡ በቫይረሱ እየተጠቁ ካሉት የማህበረሰብ ክፍሎች መካከል ደግሞ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደሆኑ ጥናቶቹ ያሳያሉ፡፡

 
  
መንግስቴ ረብሶ (ዶ/ር)

                                                             
እያንዳንዳችን ደማችን በመመርመር ያለንበትን ሁኔታ እስካላወቅን ድረስ ከቫይረሱ ነጻ ነን ማለት ስለማንችል ተማሪዎቻችን በፈቃደኝነት የኤች አይ ቪ ኤድስ ደም ምርመራ በማድርግ ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ እንዳለባቸዉ ለማሳሰብ እወዳለሁ፡፡ አብዛኛዉን ጊዜ በዩኒቨርሲቲ ዉስጥ የሚማሩ ወጣቶች ለኤች አይ ቪ እና ስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች የተጋለጡ የማህበረሰብ ክፍሎች መሆናቸዉ ይታወቃል፡፡ ወጣቶችን ለኤ ች አይ ቪ እና ስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ከሚያጋልጧቸዉ ምክንያቶች በዋናነት ያለቅድመ ዝግጅት ወሲብ እንዲፈጽሙ የሚያደርግ የአቻ ግፊት ፣ ጥንቃቄ ወደ ጎደለዉ ወሲብ የሚመሩ አጋላጭ ሁኔታዎች (ለምሳሌ፡- ጫት፣ አልኮል፣ ሃሺሽ፣ ወሲብ ተኮር ፊልሞችና ድረ - ገጾችን ማየት)፣  ለአንድ ወንድ/ ሴት ጓደኛ ታማኝ አለመሆን፣ በርካታ የወሲብ አጋሮች መኖር፣ ግብረስጋ ግንኙነት በሚፈጽሙበት ጊዜ ኮንዶም አለመጠቀም፣ ከሴተኛ አዳሪዎች ጋር ወሲብ መፈጸም ወዘተ ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡
ስለሆነም ተማሪዎቻችን ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጡ ዋና ዓላማቸዉ ትምህርት እና ትምህርት ብቻ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም ጤነኛ እና ዉጤታማ አገር ተረካቢ አምራች ሃይል ሆነዉ እንዲወጡ ከላይ የጠቀስኳቸዉን ለኤች አይ ቪ እና ስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች  አጋላጭ ሁኔታዎችና ባሪያት ራሳቸዉን በመጠበቅ ወይም በመቆጠብ ከቫይረሱ ነጻ ሆነዉ ትምህርታቸዉን በስኬት ማጠናቀቅ ይችላሉ፡፡ በዩኒቨርሲቲዉ ዉስጥ የኤች አይ ቪ ኤድሰ እና ስነተዋልዶ ጤና ችግሮች ለመከላከል ተማሪዎቻችን መታቀብ፣ መታመን፣ ኮንዶምን በአግባቡና በቋሚነት መጠቀም፣ ከአደጋ ተጋላጭነት ወደራቁ ጓደኞች ማዘንበል፣ ለፍቅር አጋር የወሲብ ታሪክን በፍጹም ታማኝነትን መናገር፣ በማይመች አደገኛ ሁኔታ ዉስጥ ሲሆኑ አላስፈላጊ ግፊትን መቋቋም፣ ለወደፊት ህይወት ማቀድና ግልጥ የሆነ የህወት ግብ ማስቀመጥ፣ የኤች አይ ቪ ምክርና ምርመራ ማድረግ፣ ጫት፣ አልኮል፣ ሃሺሽ እና አደገኛ ዕጾችን አለመጠቀም፣ ወሲብ ተኮር ፊልሞችና ድረ - ገጾችን አለማየት እና አገልግሎቶችን መፈለግ እንዳለባቸዉ ላሳስባቸዉ እወዳለሁ፡፡
አሁንም ትኩረት ለኤች አይ ቪ መከላከል!

መንግስቴ ረብሶ (ዶ/ር)                                                               
የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ኤች አይ ቪ ኤድስ እና ስነ ተዋልዶ ጤና ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሃላፊ

ከልብ እናስባለን!


Posted by Mekelle University Alumni Director Office at 7:29 AM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Tuesday, December 11, 2018

13ኛው የብሔር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በመቐለ ዩኒቨርስቲ በደምቀት ተከብሯል።

     የኢትዮጵያዊነት ተምሳሌት የኣንድነት ምስክር የሆነው መቐለ ዩኒቨርስቲ ዛሬም እንደወትሮው 13ኛ የብሔር፣ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዛሬው እለት መነሻ ዋና ግቢ በማድረግ 1:30 በሚወስድ የእግር ጉዞ እንዲሁም የከተማውን ፅዳት በማከናወን "በብዝሃነት የደመቀ ኢትዮጵያዊ ኣንድነት" በሚል መሪ ቃል በኣድሓቂ ግቢ ኣክብረነዋል።


ኣዘጋጅ፥ግደይ ልኡል 
Posted by Mekelle University Alumni Director Office at 8:30 AM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Free Access link to download any Book


Subject: Springer Nature eBook – Accessible freely 
Ministry of Science and Higher Education has subscribed Springer Nature
          published materials which avail more than 70,000 eBooks in all fields of study
          to all government Universities in Ethiopia. 
You can download the entire book or chapter by chapter and save it, print it etc.
         without restriction.Please use  those remarkable resources  and 
    pass the information so that it can be accessed  by the University staffs and students.
Please follow the steps here under for perpetual access.
  1. On the URL write --- link.springer.com
  2. Browse by discipline study will appear

  3. Double click on the subject of your choice
  4. different e-books document links will appear
  5. On the top click on Date published write on between 2005 and 2016.
  6. At the top left side, you find include preview only and unthicken the thick mark
  7.  Click on the book title you want
  8. At the right side at the top you can find download PDF as you click it get the
                      full text of the book you want to access or print or store at any storage media.

______________________________________________________________

    Mekelle University Student Union
    Gidey Leul , SU President
 
 Contact us please via

Email:                           gideyleul@gmail.com

  • Twiteer                     https://twitter.com/gideyleul
  • (Twitter)

      • youtube chanel      https://www.youtube.com/channel/UC1-khAOyBgkGdJVXI3sw7QA
      • (YouTube)
      • Instagram              https://www.instagram.com/gideyle/
      • (Instagram)
      • Facebook               https://www.facebook.com/gideyl143
    Posted by Mekelle University Alumni Director Office at 1:00 AM 2 comments:
    Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

    Monday, December 10, 2018

    በመ.ቴ.ኢ ግቢ የኮምፒተር ሳይንስ እና ምህንድስና ትም/ት ክፍል የስርዓተ_ትምህርት ማሻሻያ ግምገማ(National workshop)ኣካሄደ።

            በመ.ቴ.ኢ ከሚገኙት ተፅዕኖ ፈጣሪ የትምህርት ዘርፎች ኣንዱ የሆነው የኮምፒተር ሳይንስ እና ምህንድስና ትም/ት ክፍል በዛሬው ዕለት ህዳር 29 ከተለያዩ ኣንጋፋ የሀገራችን ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ምሁራን በተሳተፉበት የግማሽ ቀን መድረክ እጅግ ስኬታማ የስርዓተ_ትምህርት ማሻሻያን ኣከናውኗል።
             የግቢው ዲን መምህር መለስ ለተጋባዥ እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መለእክት በማስተላለፍ ፕሮግራሙን በይፋ የከፈቱት ሲሆን የካሪክለም ግምገማ ቡድን ኣስተባባሪ የሆኑት መምህር ኣክሊል ዘነበ የስርዓተ ትምህርቱ ማሻሻል ኣስፈላጊነት እና ኣላማ ለተሳታፊዎች ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት ተሳታፊዎቹ ላነሷቸው ጥያቄዎችም በማመስገን ሁሉም እንደ ግብኣት ወስደን እንሰራበታለን ብለዋል።  
           መ.ቴ.ኢ በ16 ኣመታት ጉዞው የስርዓተ ትምህርት ማሻሻያ ሲያደርግ ይህ የመጀመሪያው ነው። የኮምፒተር ሳይንስ እና ምህንድስና ትም/ት ክፍል ጨምሮ የኮሚኒኬሽን እና ምህንድስና፣የኤለክትሪካል ምህንድስና፣የኬሚካል ምህንድስና እና የኣይ ቲ ትምህርት ክፍሎች ተመሳሳይ ምድረክ ማካሄዳቸው ይታወሳል።        
      






    Posted by Mekelle University Alumni Director Office at 10:24 AM 2 comments:
    Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

    Tuesday, December 4, 2018

    _ህዳር 24፣2011ዓ.ም_
    የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት ከኣዲስኣበባ ኣቻችን ጋር የልምድ ልውውጥ ኣደርገናል።
    ***************************
    የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት ከኣዲስኣበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት በሁለንተናዊ የዩኒቨርስቲዎቹ እንቅስቃሴዎች የጋር ልምድ ልውውጥ ኣደርገናል።
          🌅 የማህበረሰብ ኣገልግሎቶች (ኣረጋውያን መርዳት፣ሜኒቶሪንግ)
          🌅 የዩኒቨርስቲያችን ሰላም ማስጠበቅ
         🌅 በኣደንዛዥ ሱስ እና ኣልኮል 
        📌ዴሞክራሲያዊ የኣስተማሪ እና ተማሪ ግንኙነት
         📌የኮሚቴዎች እንቅስቃሴ እና በሌሎች ርእሶች ፣6ኪሎ በሚገኘው የህብረቱ ዋና ፅ/ቤት በማረፍ ሰፊ የሁለትዮሽ ውይይት                 ኣድርገናል።
       




    Posted by Mekelle University Alumni Director Office at 1:20 PM 1 comment:
    Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

    Friday, November 30, 2018

    በመቐለ ዩኒቨርስቲ ለድህረ ምረቃ ተማሪዎች ቅበላ ተደረገ።


    #መቐለ_ዩኒቨርስቲ
    ከሶማሊላንድ ሀርጌሳ ዩኒቨርስቲ ለድህረ ምረቃ ትምህርት ለመጡ ተማሪዎች ደማቅ ኣቀባበል ተደረገ።
    *******************************
    የድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን ለመከታተል ከሶማሊላንድ ሃርጌሳ ዩኒቨርስቲ ለመጡ 68 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ህዳር 20፣ የመቐለ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ በተገኙበት በቃላሚኖ ግቢ ደማቅ ኣቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን የኮሌጁ ዲን ደ.ር በሪሁ ገብረኪዳን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ኣስተላልፈዋል። 
              የኣካዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር ደ.ር ታደሰ እንደገለፁት ዩኒቨርስቲያችን በኣጠቃላይ 333 የትምህርት ፕሮግራሞች እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን ከሀገራችን ግብርና ወደ ኢንዳስትሪ መር በሚደረገው ሽግግር እጅግ ኣስፈላጊ እና በመቐለ ዩኒቨርስቲ ብቻ የሚሰጡ (ካይዘን ኢንስቲትዩት፥ ክላይሜት ሜትሮሎጂ፣ ፔትሮሊየም ኢንጂነሪንግ) ጨምሮ በኣለም ኣቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እና በርካታ የማህበረሰብ ችግሮች በሚፈቱ (Need Based Diversification) 40 የPHD ፕሮግራሞች እየሰጠ ይገኛል። 20ዎቹ በዚሁ ኣመት የተጀመሩ ፕሮግራሞች ናቸው። 
                    ዩኒቨርስቲው ከሶማሊላንድ መንግስት፣ከምስራቅ ኣፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት(IGAD)፥ ደቡብ ሱዳን፥ጋና እና ሌሎች ሀገሮች ጨምሮ በርካታ ተማሪዎች እያስተናገደ ይገኛል። 
    ኣዘጋጅ፥ ግደይ ልኡል
          




         
      

    Posted by Mekelle University Alumni Director Office at 3:44 AM No comments:
    Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest
    Newer Posts Home
    Subscribe to: Comments (Atom)

    About Me

    Mekelle University Alumni Director Office
    View my complete profile

    Blog Archive

    • ►  2025 (2)
      • ►  March (2)
    • ►  2019 (4)
      • ►  December (2)
      • ►  August (1)
      • ►  February (1)
    • ▼  2018 (10)
      • ▼  December (9)
        • Drop of Water Club has Provided 45 Installed water...
        • የዓይደር ግቢ ተማሪዎች ፓርላማ የሩብ ኣመት ጠቅላላ ጉባኤ ኣካሄደ።
        • መቐለ ዩኒቨርስቲ ከትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በመተባበር በሀገራችን ወቅታ...
        • በመ.ቴ.ኢ ግቢ ለተመራቂ ተማሪዎች ስልጠና ተሰጠ።
        • የኤች.ኣይ.ቪ/ኤድስ ሳምንት በመቐለ ዩኒቨርስቲ እየተከበረ ይገኛል በዓሉ በማስመ...
        • 13ኛው የብሔር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በመቐለ ዩኒቨርስቲ በደምቀት ተከብሯል።
        • Free Access link to download any Book
        • በመ.ቴ.ኢ ግቢ የኮምፒተር ሳይንስ እና ምህንድስና ትም/ት ክፍል የስርዓተ_ትምህ...
        • _ህዳር 24፣2011ዓ.ም_ የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት ከኣዲስኣበባ ኣ...
      • ►  November (1)
        • በመቐለ ዩኒቨርስቲ ለድህረ ምረቃ ተማሪዎች ቅበላ ተደረገ።
    Picture Window theme. Powered by Blogger.