Monday, December 10, 2018

በመ.ቴ.ኢ ግቢ የኮምፒተር ሳይንስ እና ምህንድስና ትም/ት ክፍል የስርዓተ_ትምህርት ማሻሻያ ግምገማ(National workshop)ኣካሄደ።

        በመ.ቴ.ኢ ከሚገኙት ተፅዕኖ ፈጣሪ የትምህርት ዘርፎች ኣንዱ የሆነው የኮምፒተር ሳይንስ እና ምህንድስና ትም/ት ክፍል በዛሬው ዕለት ህዳር 29 ከተለያዩ ኣንጋፋ የሀገራችን ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ምሁራን በተሳተፉበት የግማሽ ቀን መድረክ እጅግ ስኬታማ የስርዓተ_ትምህርት ማሻሻያን ኣከናውኗል።
         የግቢው ዲን መምህር መለስ ለተጋባዥ እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መለእክት በማስተላለፍ ፕሮግራሙን በይፋ የከፈቱት ሲሆን የካሪክለም ግምገማ ቡድን ኣስተባባሪ የሆኑት መምህር ኣክሊል ዘነበ የስርዓተ ትምህርቱ ማሻሻል ኣስፈላጊነት እና ኣላማ ለተሳታፊዎች ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት ተሳታፊዎቹ ላነሷቸው ጥያቄዎችም በማመስገን ሁሉም እንደ ግብኣት ወስደን እንሰራበታለን ብለዋል።  
       መ.ቴ.ኢ በ16 ኣመታት ጉዞው የስርዓተ ትምህርት ማሻሻያ ሲያደርግ ይህ የመጀመሪያው ነው። የኮምፒተር ሳይንስ እና ምህንድስና ትም/ት ክፍል ጨምሮ የኮሚኒኬሽን እና ምህንድስና፣የኤለክትሪካል ምህንድስና፣የኬሚካል ምህንድስና እና የኣይ ቲ ትምህርት ክፍሎች ተመሳሳይ ምድረክ ማካሄዳቸው ይታወሳል።        
  






2 comments: