በመቐለ ዩኒቨርስቲ የስራ ማእከል ዳይሬክተር ፅ/ቤት
የተዘጋጀ የኣቅም ግንባታ ስልጠና ለተመራቂ ተማሪዎች ታህሳስ 3,2011ዓ.ም በመ.ቴ.ኢ ግቢ ተሰጥቷል።
መቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት
በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጽ/ቤቱ ዳይሬክተር ደ/ር ግርማይ
እንደገለጹት በተያዘው ኣመት በተመራቂ ተማሪዎች ዘርፈ ብዙ የክህሎት ማሳደጊያ ስልጠናዎች እና የስራ ፈጠራ ተሞክሮዎች በመስጠት ተወዳዳሪ እና ብቃት ያላቸው ተማሪዎች ለማፍራት እንዲሁም ለኣጋር ካምፓኒዎች ተቋማት እንዲጎበኙ ክፍት ለማድረግ ዝግጅታችን
ጨርሰናል ብለዋል። ኣክለውም የካሬር ችለብ በዚህ ወር ይቋቋማል።።
ስልጠናው መሰረታዊ የክህሎት ማዳበር በማተኮር በcv ኣጻጻፍ፣ የኣፕሊኬሽን
ደብዳቤ ኣዘገጃጀት እና ቃለ መጠይቅ ኣቀራረብ ዙርያ በወ/ሮ ብርሃን የፅ/ቤቱ መማክርቱ ሰፊ ስልጠና የሰጡ ሲሆን የካሬር እና ጆብ
ፌር መድረኮች በማዘጋጀት፣ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች በተለያዩ የኢንተርኔት ስኮላር ሺፖች እና ፈለውሽፖች የሚያመለክቱበትና የሚወዳደሩበት
የክህሎት ስልጠናዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።
ይህ የክህሎት ግንባታ ስልጠና ለ2ኛ ግዜ ሲሆን ለቅዳሜ
ታህሳስ 6,2011ዓ.ም ደግሞ በቃላሚኖ ግቢ ለሚገኙ ተመራቂ ተማሪዎች የሚቀጥል ይሆናል።


No comments:
Post a Comment